Search
የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ጥቅምት 20 2018
የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡
ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበልና በማጣራት እንዲሁም አስተዳደራዊ በደሎች መፈፀማቸውን ሲያረጋግጥ ማስተካከያ እንዲደረግ ለተቋማት ምክረ ሃሳቦችን ይሰጣል፡፡
ቅሬታ የቀረበባቸው ተቋማት አሰራሩ እንደሚፈቅደው በ1ወር ጊዜ ውስጥ ምክረ ሃሳቡን መፈፀማቸውን ወይም አለመፈፀማቸውን ከእነምክንያቱ ለእምባ ጠባቂ ተቋም ማሳወቅ እንዳለባቸው የተቋሙ ምክትል እምባ ጠባቂ የኔነህ ስመኝ (ዶ/ር )ነግረውናል።
ምክረ ሃሳቡን ተቀብለው ማስተካከያ የሚያደርጉ ተቋማት እንዳሉ ሁሉ ያለ በቂ ምክንያት ለአቤት ባዮች ቅሬታ ምላሽ የማይሰጡ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ እንደሚደረግ የሚያነሱት ሃላፊው ይሁንና የእምባ ጠባቂ ተቋምን ምክረ ሃሳብ ያለመፈፀም ወንጀል በመሆኑ ለአቃቢ ህግ ክስ እንዲመሰረት ብንልክም ጉዳዩን እንደ ሌላ ወንጀል እንዲጣራ ወደ መርማሪ ፖሊስ የሚልኩት በመሆኑ ስራችን ላይ እንቅፋት እየፈጠረ ነው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1h ago
4:38
0
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
5h ago
3:13
6
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
5h ago
2:33
1
በትምህርት ሥርዓቱ አይነ ስውራን ከማይማሯቸው የት/ት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀት የሚያገኝበት አይሲቲ አንዱ ነው፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
6h ago
5:07
3
ከዚህ ቀደም በገላን ሁለገብ ደረቅ ወደብ የደረሱ እቃዎችን እዛው የጉምሩክ ሥርዓት ማስፈፀም ሲገባ ለጉምሩክ ሥርዓት ሲባል ብቻ ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ እቃዎች በከባ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
6h ago
4:57
26