Search
የቤተሰብ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ32ተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ3ተኛ ጊዜ ዛሬ ግንቦት 7 2017 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የቤተሰብ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ32ተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ3ተኛ ጊዜ ዛሬ ግንቦት 7 2017 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የቤተሰብ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ32ተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ3ተኛ ጊዜ ዛሬ ግንቦት 7 2017 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ግንቦት 7 2017
የፍቺ ቁጥርን ለመቀነስ የቅድመ የጋብቻ ስልጠና እየሰጠሁ ነው ሲል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
ይህ የተባለው ዛሬ ለሚከበረው የቤተሰብ ቀንን አስመልክቶ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡
በዚህም ሰዎች ለፍቺ ከመዳረጋቸው አስቀድሞ ወደ ትዳርም ከመግባታቸው በፊት የተለያዩ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱና የምክር አገልግሎት እንደሚሰጣቸው ከተቋሙ ሰምተናል፡፡
ይህም ወደ ትዳር ከገቡ በኋላ የሚገጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት ያግዛቸዋል ተብሏል፡፡
ስልጠናው የሚሰጠው ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት ወደ ትዳር ከገቡ በኋላና በትዳር ላይ ሆነው የሚወስዱት እንደሆነ የተናገሩት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ሁርያ አሊ ናቸው፡፡
ከቤተሰብ አካላት መካከል የሆኑት ህፃናት ሴቶች የአካል ጉዳተኞች እንዲሁም አዛውንቶች የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሆነ ሚኒስትር ድኤታዋ ተናግረዋል፡፡
በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ምክንያት ችግር ለሚደርስባቸው ሰዎችም ከተለያዩ ረጅ ተቋማት ጋር በመሆን ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነም ሰምተናል፡፡
ይሁንና ድጋፉ የሚገባቸው እያሉ ያልተገባቸው ይወስዱ እንደነበር እና ይህንን ለማስተካከል የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት መዘርጋቱንም አስረድተዋል፡፡
የቤተሰብ ቀን የተሻሻለ የቤተሰብ ገቢ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ በሚል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ32ተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ3ተኛ ጊዜ ዛሬ ግንቦት 7 2017 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል፡፡
ማርታ በቀለ
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:00
8
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
2:33
3