Search
የፌዴራል መ/ቤቶች አጀንዳዎቻቸውን ለምክክር ኮሚሽን የሚያቀርቡበት የምክክር መድረክ ግንቦት 8/2017 በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል ተባለ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የፌዴራል መ/ቤቶች አጀንዳዎቻቸውን ለምክክር ኮሚሽን የሚያቀርቡበት የምክክር መድረክ ግንቦት 8/2017 በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል ተባለ
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የፌዴራል መ/ቤቶች አጀንዳዎቻቸውን ለምክክር ኮሚሽን የሚያቀርቡበት የምክክር መድረክ ግንቦት 8/2017 በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል ተባለ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ሚያዝያ 21 2017
የህዝብ ተወካዮች፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት፣ የመከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል መስሪያ ቤቶች አጀንዳዎቻቸውን ለምክክር ኮሚሽን የሚያቀርቡበት የምክክር መድረክ ግንቦት 8/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል ተባለ፡፡
ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል በተባለው የፌዴራል ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ በተወካዮቻቸው በኩል አጀንዳዎቻቸውን ለምክክር ኮሚሽን እንደሚያቀርቡ ተነግሯል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቃባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ከሳምታት በኋላ መካሄድ በሚጀምረው የምክክር መድረክ ላይ የህግ አውጪው፣ ህግ ተርጓሚው እና ህግ አስፈጻሚው አካላት በምክክሩ ይሳተፋሉ፤ አጀንዳዎቻችን ናቸው ያሉትንም ለኮሚሽኑ ያስረክባሉ ብለን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡
መድረኩ፤ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የሀይማኖት፣ የፀጥታ፣ የፍትህ ተቋማት እና ሌሎች የፌዴራል ተቋማት ለሶስት ቀናት መክረው አጀንዳዎቻቸውን የሚያቀርቡበት ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ከዚህ በፊት በክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉ የህብረተሰብ ከፍሎች በዚህኛው መድረክ አይሳተፉም ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በተካሄዱ የምክከር መድረክ ላይ የተሳተፉ የህብረተሰብ ከፍሎች ማለትም የሃይማኖት ተቋማት፣ የንግድ ማህበረሰብ፣ የእድር፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የመምህራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የተፈናቃይ ህብረተሰብ ተወካዮች አጀንዳዎቻቸውን ማስረከባቸውን የጠቆሙት አቶ ጥበቡ ታደሰ በፌደራል ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ ግን እነዚህ አካላት እንደማይሳተፉ ነግረውናል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4