Search
የመንግስት የወጪ ፍላጎት በገቢ አቅሙ መሸፈን አለበት የሚል ጠንካራ አቋም መያዙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የመንግስት የወጪ ፍላጎት በገቢ አቅሙ መሸፈን አለበት የሚል ጠንካራ አቋም መያዙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የመንግስት የወጪ ፍላጎት በገቢ አቅሙ መሸፈን አለበት የሚል ጠንካራ አቋም መያዙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ሰኔ 24 2017
የመንግስት የወጪ ፍላጎት በገቢ አቅሙ መሸፈን አለበት የሚል ጠንካራ አቋም መያዙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ።
ሚኒስትሩ በ2018 የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ዙሪያ ዛሬ ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
የ2018 የፌዴራል መንግስት ጠቅላላ ወጪ በጀት 1.93 ትሪሊየን ብር ሆኖ መዘጋጀቱ ይታወሳል።
ከተያዘው አጠቃላይ በጀት 1.2 ትሪሊየን ብር ለመደበኛ ወጪ፣ 415.2 ቢሊየን ብር ለካፒታል ወጪ፣ 315 ቢሊየን ብር ለክልሎች የበጀት ድጋፍ እና 14 ቢሊየን ብር ለክልሎች የዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የተደለደለ እንደሆነ ተነግሯል።
ለአመቱ ከተያዘው 1.93 ትሪሊየን ብር ውስጥ 1.23 ትሪሊየን ብር ታክስ እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ይሰበሰባል ተብሎ ግብ ተቀምጧል።
ለዓመቱ በተዘጋጀው ረቂቅ በጀት ዙሪያ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ውይይት ተካሂዷል።
የምክር ቤቱ አባላትም የተለያዩ ጥያቄዎችን በረቂቅ በጀቱ ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠት ለተገኙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አቅርበዋል።
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:00
8
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
2:33
3