Search
በ12 ባለሃብቶች ከንጋት ሃይቅ 3.8 ሚሊዮን ኪሎ ግራም አሳ መመረቱ ተነገረ፡፡ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
በ12 ባለሃብቶች ከንጋት ሃይቅ 3.8 ሚሊዮን ኪሎ ግራም አሳ መመረቱ ተነገረ፡፡
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በ12 ባለሃብቶች ከንጋት ሃይቅ 3.8 ሚሊዮን ኪሎ ግራም አሳ መመረቱ ተነገረ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
የካቲት 16/2018
በ12 ባለሃብቶች ከንጋት ሃይቅ 3.8 ሚሊዮን ኪሎ ግራም አሳ መመረቱ ተነገረ፡፡
በሃይቁ ካለው ከፍተኛ የአሳ ምርት አንፃር አሁንም ቢሆን በበቂ መጠን እየተመረተ አይደለም ተብሏል። ተጨማሪ ባለሃብቶች ወደ ስራው እንዲገቡም ጥሪ ቀርቧል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ በፈጠረውና ንጋት በሚል ስያሜ በሚጠራው ሰው ሰራሽ ሃይቅ የሚድሮክ ኤትዮጵያ አካል የሆነው ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪን ጨምሮ 12 ባለሃብቶች ከጉባ አካባቢ ወጣቶች ጋር በመሆን በዚህ ዓመት 3ሺህ 895 ቶን ወይም 3.8 ሚሊዮን ኪሎ ግራም አሳ አምርተው ለገበያ ማቅረባቸውን ሰምተናል፡፡
ባለሃብቶቹ ለአሳ ምርት አስፈላጊ የሆኑ የማስገሪያ ማሽነሪዎችንና ምርቱን ለማጓጓዝ የሚሆኑ ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸው ተሽከርካሪዎችን በማቅረብ ወደ ስራው መግባታቸውን ግድቡ የሚገኝበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ የአሳ ሃብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ቡሼን ቡፋ ነግረውናል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ኢትዮጵያ በመጪው አመት ከምታዘጋጀው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በተጓዳኝ ለሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውንና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ የሚያተኩር ዓለም አቀፍ አውደ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3h ago
4:42
4
በሀብት ሽሚያ ምክንያት በተለይ ጋምቤላ አካባቢ በነዋሪው እና በአካባቢው በተጠለሉ ስደተኞች መካከል ግጭት የተፈጠረባቸው ተደጋጋሚ ክስተቶች መታየታቸው ይነገራል
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
4h ago
3:38
1
የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው እና ቀዳሚው ነፃ የንግድ ቀጠና ሆኖ ስራ ከጀመረ ከአራት አመት በላይ ሆኖታል።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
4h ago
5:37
4
ለትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘርነት ወንድ እና ሴት ተወዳዳሪዎች እኩል ውጤት ካመጡ ለሴት ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ እንድታልፍ የሚያደርግ መ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
5h ago
3:45
3
የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን የከተማዋን የመጠጥ ውኃ ችግር ለመፍታት 2.2 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል አለ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
6h ago
4:17
8