Search
በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል የቀጠለው ውጥረት ወደ ጦርነት እንዳያመራ ሁሉም ዓይነት የሰላም ጥረቶች እንዲቀጥሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል የቀጠለው ውጥረት ወደ ጦርነት እንዳያመራ ሁሉም ዓይነት የሰላም ጥረቶች እንዲቀጥሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል የቀጠለው ውጥረት ወደ ጦርነት እንዳያመራ ሁሉም ዓይነት የሰላም ጥረቶች እንዲቀጥሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ጥቅምት 25 2018
በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል የቀጠለው ውጥረት ወደ ዳግም አውዳሚ ጦርነት እንዳያመራ ሁሉም ዓይነት የሰላም ጥረቶች እንዲቀጥሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል፡፡
የሰሜን ዕዝ የተጠቃበትን 5ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተሰናዳ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ህወሓት ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ያደረጋቸው “ትንኮሳዎች፣ እምቢ ባይነቶች፣ ስራዎች እና ሴራዎች” ወደ ጦርነት ለመግባት ከበቂ በላይ መሆነቸውን ተናግረው እኛ ምንም ብንታገስ ከተጠቃን ግን መከላከላችን አይቀርም ሲሉ ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እኛ ብቻ ጦርነትን ማስቀረት አንችልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህን አስመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ ሊቀመንበር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (ዶ/ር) ዳግም ጦርነት እንዳይነሳ እንዲሁም የውጭ ሃይል ጣልቃ ገብነትን ለማስቀረት ድርድር እና ሽምግልናን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት የሰላም ጥረቶች እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ(ኦፌኮ) ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸው የህዝብን ሃብት እና ወጣቱን አላማ ለሌለው ጦርነት ማዋል በምንም መመዘኛ አግባብነት እንደሌለው ሁለቱም አካላት ማወቅ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1h ago
4:38
0
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
4h ago
3:13
6
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
5h ago
2:33
1
በትምህርት ሥርዓቱ አይነ ስውራን ከማይማሯቸው የት/ት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀት የሚያገኝበት አይሲቲ አንዱ ነው፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
5h ago
5:07
3
ከዚህ ቀደም በገላን ሁለገብ ደረቅ ወደብ የደረሱ እቃዎችን እዛው የጉምሩክ ሥርዓት ማስፈፀም ሲገባ ለጉምሩክ ሥርዓት ሲባል ብቻ ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ እቃዎች በከባ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
5h ago
4:57
26