Search
''በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩት ላይ ጥቆማ እየደረሰን በመሆኑ በአዘዋዋሪዎቹ ላይ እርምጃ አየተወሰደባቸው ነው'' by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
''በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩት ላይ ጥቆማ እየደረሰን በመሆኑ በአዘዋዋሪዎቹ ላይ እርምጃ አየተወሰደባቸው ነው''
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
''በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩት ላይ ጥቆማ እየደረሰን በመሆኑ በአዘዋዋሪዎቹ ላይ እርምጃ አየተወሰደባቸው ነው''
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
መጋቢት 18 2017
በደላሎች አማካኝነት ለህገወጥ ስደት ሰለባ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን እስከ ሞት የደረሰ የተለያየ ችግር እንደሚጋጥማቸው ተደጋግሞ ይነገራል፡፡
በተለይ ለዚህ ችግር ተጋላጭ ናቸው የተባሉትን ሴቶችን በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ በማገዝ ህገወጥ ስደትን ከስሩ ለማስቀረት እየሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር እርጎጌ ተስፋዬ በህገወጥ መንገድ ወይንም መደበኛ ባልሆነ መልኩ የሚፈልሱት አብዛኞቹ ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውን አንስተው በተለይ ሴቶች የዚሁ ሰለባ እንዳይሆኑ በሚል በገጠር አካባቢ ያሉትን በግብርናው ዘርፍ ተሰማርተው የሚሰሩበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ለህገወጥ ወይንም መደበኛ ላልሆነ ፍልሰት ብዙዎቹ የሚጋለጡት ከድህነት ባለፈ በሀገሪቱ ባለው ግጭቶች ሳቢያ እንደሆነም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩት ላይ ጥቆማ እየደረሰን በመሆኑ በአዘዋዋሪዎቹ ላይ እርምጃ አየተወሰደባቸው ነውም ብለዋል።
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4