Search
''ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አለመወሰኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በተለያዩ ፋብሪካዎች የሚሰሩ የሠራተኞች ላይ ችግር ፈጥሯል'' ኢሰመኮ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
''ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አለመወሰኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በተለያዩ ፋብሪካዎች የሚሰሩ የሠራተኞች ላይ ችግር ፈጥሯል'' ኢሰመኮ
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
''ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አለመወሰኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በተለያዩ ፋብሪካዎች የሚሰሩ የሠራተኞች ላይ ችግር ፈጥሯል'' ኢሰመኮ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ሚያዝያ 23 2017
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አለመወሰኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በተለያዩ ፋብሪካዎች የሚሰሩ የሠራተኞች ላይ ችግር ፈጥሯል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡
በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሸገር ሲቲና ሃዋሳ ከተሞች በሚገኙ ኢንደስትሪ ፓርኮችና ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰሩ የሴት ሰራተኞች መብቶች አያያዝን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ጋር ዉይይት አድርጓል፡፡
ኮሚሽኑ በዚህ ጉዳይ ሶስት ዙር ክትትል ማድረጉን በዚህም የተሻሻሉና የቀጠሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን አግኝቻለሁ ብሏል፡፡
በጤና አጠባበቅ ዙሪያ የግብዓቶች አለመሟላት፣ የደመወዝ ጉዳይ፣ የፀረ ትንኮሳ ፖሊሲ አለመኖርና ሌሎችም የቀጠሉ ናቸው መባሉንም ሰምተናል፡፡
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ላይ ያሉ መብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ክፍተቶች መታየታቸውን ተነግሯል፡፡
ይህም ሆኖ መሻሻል የታየባቸው ጉዳዮች እንዳሉም ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሰምተናል
ሴቶች የወሊድ ጊዜ እረፍት ከክፍያ ጋር ማግኘት ሲገባቸው ይህ መብት ሳይረጋገጥ መቅረቱንም ኢሰመኮ ተመልክቻለው ብሏል፡፡
ከሁሉም በላይ አሳሳቢው ደግሞ መንግስት ዝቅተኛ የሆነ የደመወዝ ወለል ባለመወሰኑ ችግር ያመጣል ሲሉ የተናገሩት የኢሰመኮ የሴቶች፣ የህፃናት፣ የአረጋዊያንና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋርያ ናቸው፡፡
ሌላኛው አሳሳቢ ጉዳይ በሀዋሳ እና በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሁሉም ፋብሪካዎች የአደጋ መከላከያዎች እና የጤና መጠበቂያ ቁሳቁሶች በበቂ ሁኔታ አለመሟላታቸው ነው ብሏል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4