Search
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ግንቦት 6 2017
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
ጉባኤው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ አፈጻጸም በመገምገም ለቀጣዩ ጊዜ የስራ መመሪያ የሚቀመጥበት ነው፡፡
በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በንግግራቸው፤ እኛ መንፈሳዊ አባቶች ለሕዝበ እግዚአብሔር የምናበረክተው አገልግሎት በመንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚና በማህበራዊውም ጭምር ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ አንፃር ህዝቡ የተሻለ ማኅበራዊ አገልግሎት እንዲያገኝ፣ በኢኮኖሚውም ከድህነት የተላቀቀ እንዲሆን እንደሁም ሰላሙና አንድነቱ የተጠበቀ እንዲሆን በማስተማርም በተግባር በመሳተፍም የሕዝቡ መሪና አርዓያ ሆነን መስራት ይገባናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ከሰላም እጦት የተነሣ በእጅጉ እየተጎዳ ያለውን ሕዝቡ ሰላምና ፍትሕ እንዲያገኝ በጸሎትም በትምህርትም፣ በምክርም ተግተን መስራት አለብን ያሉት ፓትሪያርኩ፤ ለእንግልት እየተዳረገ ያለውም በዋናነት በገዛ ልጆቹ ነው፤ እናት በገዛ ልጆቿ ስትንገላታ ማየት እጅግ አሳዛኝ ነገር ነው፤ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ልማትና ዕድገት እናሻግራለን ብላችሁ እየደከማችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን እባካችሁ ሁሉን የሚያግባባ ነገር ፈልጉና ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ፍቱ ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ ተደራሽነት በሳሳባቸው አካባቢዎች በሙሉ በተለየ ትኩረት በመስራት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ይኖርብናል ያሉት አቡነ ማቲያስ በተለያዩ ምክንያቶች ከሲኖዶሱ የወጡ ምዕመናንን ወደ ሲኖዶሱ እንዲመለሱ መስራት የጉባኤው ተቀዳሚ ተልዕኮ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:00
8
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
2:33
3