Search
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት በአራት ዕጥፍ ጨምሮ እንዲሻሻል መደረጉ ይታወሳል by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት በአራት ዕጥፍ ጨምሮ እንዲሻሻል መደረጉ ይታወሳል
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት በአራት ዕጥፍ ጨምሮ እንዲሻሻል መደረጉ ይታወሳል
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት በአራት ዕጥፍ ጨምሮ እንዲሻሻል መደረጉ ይታወሳል፡፡
ይህ በየጊዜው እንዲሻሻል ሲጠየቅ የነበረው የምግብ በጀት መሻሻሉ መልካም ሆኖ እያለ የምግብ በጀት ተመን በጨመረው ልክ የወጪ መጋራት ላይ የሚጨመረው ክፍያ በሌላ በኩል ስጋት እንደፈጠረባቸው ተማሪዎች ነግረውናል፡፡
ይህ መሆኑ በሀገሪቱ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ለተመራቂዎቹ ከባድ እንደሆ የተጠቆመ ሲሆን ለዚህም መንግስት ሌሎች አማራጮችን እንደመፍትሄ ሊያይ ይገባልም ሲሉ የዘርፉ ባለሞያዎች መክረዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደ አንድ የመፍትሄ ሀሳብ በባለሙያዎች ሲቀርብ የሚሰማው ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ስለቀነሰ መንግስት መደጎም አይችልም ወይ የሚለው ነው፡፡
ስለጉዳዩ ያነጋገርናቸው በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳዳር እና የመሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብረሃ(ዶ/ር) ወደ ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ አልፎ የሚገባው ተማሪ ቁጥር ይቀንስ እንጂ፤ በአቅም ማሻሻያ የሚገባ ተማሪ ተደምሮ ከበፊቱ በጣም የራቀ የሚባል አይደለም ዩኒቨርሲቲዎች የሚቀበሉት ብለውናል፡፡
ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይ የተማሪዎች የቀን የምግብ በጀት ከነበረበት 22 ብር ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል ከመደረጉም ባሻገር፤ በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የምግብ ዝርዝር ወጥ እንዲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች ደብዳቤ ጽፎ ነበረ፡፡
ይሁን እንጂ ይህ መመሪያ ከወረደ እና የምግብ በጀት ተመኑ ከተሻሻለም በኋላ በነበረው የምግብ ዝርዝር መሰረት የቀጠሉ ዩኒቨርሲቲዎች መኖራቸውን ሰምተናል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4