Search
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮና በኦዲተርና የሂሳብ ባለሞያዎች ማህበራት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮና በኦዲተርና የሂሳብ ባለሞያዎች ማህበራት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮና በኦዲተርና የሂሳብ ባለሞያዎች ማህበራት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ሚያዝያ 14 2017
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮና በኦዲተርና የሂሳብ ባለሞያዎች ማህበራት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ አሁንም አልረገበም፡፡
ውጥረቱን ለማርገብ በማህበራቱ ለቀረበው የእንወያይ ጥያቄ ቢሮው ምላሽ እንደሰጠ ነግሮናል፡፡
የገቢ አሰባሳቢ ቢሮው ለውይይት ለመቀመጥ የማህበራቱን ህጋዊ እውቅና የሚመለከት ማስረጃ እንዲሁም የአባላቱን ዝርዝር በህጋዊ መንገድ አረጋግጣችሁ አምጡ የሚል ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን አቶ ሰውነት አስረድተዋል፡፡
ቅድመ ሁኔታውን አሟልተው ይመጣሉ ብለን እየጠበቅናቸው ነውም ብለዋል፡፡
ማህበራቱ በበኩላቸው ለቢሮው በደብዳቤ ላቀረብነው የእንወያይ ጥያቄ በደብዳቤ ምላሽ አልሰጠንም፤ይሁንና የተባለውን ቅድመ ሁኔታ እንድናሟላ በስልክ ተነግሮናል፤ በዚህ ጊዜና በዚህ ሰዓት እንወያይ የሚል ቀጠሮ ስላልተሰጠን እሱን እየጠበቅን ነው የሚል ምላሽ የሰጡን ከሶስቱ የኦዲተሮችና የሂሳብ ባለሙያዎች ማህበራት መካከል አንዱ የሆነው የውጭ ኦዲተሮች ማህበር ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሚሊዮን ማሞ ናቸው፡፡
ማህበራቱ ባሳለፍነው ሳምንት በሰጡት መግለጫ የገቢዎች ቢሮ እንዲያስተባብል የተጠየቀውን ጉዳይ በተመለከተ ምንም የማስተባብለው ነገር የለም ብሏል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4