Search
የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
መጋቢት 12 2017
በዓይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት የሚከሰት ዓይነ ስውርነትን ለማከም ከእልፈት በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡
ነገር ግን የለጋሾች ብዛት ቢጨምርም የህክምና ግብዓትና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ማነስ ብዙ እንዳይሰራ ማድረጉ ተነግሯል።
ከዚህ ቀደም የነበሩ ስራዎች በሚፈለገው መጠን አልነበሩም ተብሏል፤ አሁን ግን በተለይ ተቋሙ ራሱን ችሎ የኢትዮጵያ ደምና ህብረዋስ ባንክ በሚል ዳግም ከተቋቋመ በኋላ የተሻሻሉ ለውጦች እንደታዩ ተነግሯል፡፡
አቶ አለማየሁ ታረቀኝ የኢትዮጵያ ደመናዋስ ባንክ አገልግሎት የዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ እንደነገሩን የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ሌሎች የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በተደረገ ምክክር በኋላ የአይን ብሌናቸው ለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ይላሉ፡፡
የዓይን ብሌን በልገሳ ከተገኘ በኋላ ህክምናውን ለማድርግ የግብዓትና በዘርፉ ያሉ ቀዶ ህክምና የሚያከናውኑ ባለሙያዎች ጥቂት መሆን ብዙ እንዳይሰራ አድርጎታል ሲሉ አቶ አለማየሁ ነግረውናል፡፡
ህክምና የሚሰጡ ሀኪሞች ቁጥራቸው በጣም ትንሽ ነው ያሉን አቶ አለማየሁ አሁንም ያሉት ባለሙያዎች ቁጥር ከ12 የዘለላ አይደለም ብለዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ውጪ የዓይን ባንክ ለመክፈትና በክልሎችም አገልግሎቱን ለመስጠት በዚህ አመት የተጀመሩ ስራዎች አሉ ተብሏል፡፡
ይህም በአንድ ቦታ በማዕከል ብቻ የነበረውን አገልግሎት በማስፋት ብዙዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ተነግሯል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4