Search
በዩኤስኤአይዲ የሚደረግለት ድጋፍ በመቋረጡ ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁን የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ተናገረ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
በዩኤስኤአይዲ የሚደረግለት ድጋፍ በመቋረጡ ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁን የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ተናገረ
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በዩኤስኤአይዲ የሚደረግለት ድጋፍ በመቋረጡ ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁን የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ተናገረ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
መጋቢት 2 2017
በዩኤስኤአይዲ ( #USAID ) የሚደረግለት የገንዘብ ድጋፍ በመቋረጡ ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁን የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ተናገረ፡፡
በዚህም ምክንያት ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ የግማሽ ያህሉን የስራ ውል ለማቋረጥ መገደዱንና ፕሮጀክቶችንም ማጠፉን ማህበሩ ነግሮናል፡፡
ላለፉት 59 ዓመታት በኢትዮጵያ የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኘው ቤተሰብ መምሪያ ማህበር፤ ባሉት 46 ክኒሊኮች፣ 529 በሚደርሱ ከመንግስት ጤና ተቋማት ጋር በአጋርነት እንዲሁም ከ428 የግል የጤና ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን ነግሮናል፡፡
አቶ ጴጥሮስ ጌቼሬ በማህበሩ የክኒሊካል ሰርቪስ አገልግሎት ማናጀር ናቸው፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት የአሜሪካ መንግስት የልማት ተራድዖ ድርጅት የሆነው USAID የቤተሰብ መምሪያ በርከት ያሉ ፕሮጀክቶች ሲደግፍ ቆይቷል፡፡
ይሁንና በቅርቡ ድርጅቱ በድንገት ድጋፉን ማቆሙን ተከትሎ በገንዘብ ይደግፋቸው የነበሩ 4 ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ለማቆም ተገድደናል ብለውናል፡፡
ህልውናውን አደጋ ላይ እስከመጣል ያደረሰው ምን ያህል ገንዘብ ቢያጣ ነው ስንል የጠየቅናቸው የማህበሩ የክኒሊካል ሰርቪስ አገልግሎት ማናጀር አቶ ጴጥሮስ ጌቼሬ ያጣነው የገንዘብ መጠንም ይሁን ከስራው ምን ያህሉ ተጎድቷል የሚለው ገና በጥናት የሚለይ ነው በማለት የተወሰኑ የሚታጠፉ ስራዎችን ይጠቅሳሉ፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4