Search
የኪራይ ውል ወጪ በአዲስ አበባ በቤቶች ላይ ከፍትኛ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑ ተነገረ፡፡ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የኪራይ ውል ወጪ በአዲስ አበባ በቤቶች ላይ ከፍትኛ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑ ተነገረ፡፡
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የኪራይ ውል ወጪ በአዲስ አበባ በቤቶች ላይ ከፍትኛ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑ ተነገረ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ግንቦት 7/2018
ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት በቀሩትና በመንግስት ወጥቶ ላለፉት 2 ዓመት ሲተገበር የቆየው የኪራይ ውል ወጪ በአዲስ አበባ በቤቶች ላይ ከፍትኛ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑ ተነገረ፡፡
በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነት በህብረተሰቡ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫናና በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ በየቀኑ ሰማይ እየነካ የሄደው የዋጋ ንረት የሸማቹን የመግዛት አቅም በእጅጉ አዳክሞታል፤ ለዚህም መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ተናግሯል።
በተለይም ባለፉት 2 ዓመታት የነበሩ የኪራይ ውሎች መጠናቀቅን ተከትሎ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የኪራይ ጭማሪ በተከራዮች እየተደረገ ነው ይህንንም አረጋግጫለሁ ብሏል ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፡፡
የሸማቹ የመግዛት አቅም መዳከም ደግሞ አጠቃላይ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን አቀዝቅዞታል፤ በተጨማሪም በነዳጅ አቅርቦት፣ ስርጭት፣ እጥረትና የዋጋ ጭማሪ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ሲል ተናግሯል፡፡
ድርጅቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ባደረገው ጥናት ለኪራይ ንረቱ አሉታዊ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሁኔታዎች መታዘቡንና ጭማሪም መደረጉን ተመልክቷል ሲሉ የድርጅቱ መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ ቁምላቸው አበበ ነግረውናል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ኢትዮጵያ በመጪው አመት ከምታዘጋጀው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በተጓዳኝ ለሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውንና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ የሚያተኩር ዓለም አቀፍ አውደ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
27m ago
4:42
1
በሀብት ሽሚያ ምክንያት በተለይ ጋምቤላ አካባቢ በነዋሪው እና በአካባቢው በተጠለሉ ስደተኞች መካከል ግጭት የተፈጠረባቸው ተደጋጋሚ ክስተቶች መታየታቸው ይነገራል
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1h ago
3:38
0
የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው እና ቀዳሚው ነፃ የንግድ ቀጠና ሆኖ ስራ ከጀመረ ከአራት አመት በላይ ሆኖታል።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1h ago
5:37
3
ለትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘርነት ወንድ እና ሴት ተወዳዳሪዎች እኩል ውጤት ካመጡ ለሴት ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ እንድታልፍ የሚያደርግ መ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3h ago
3:45
3
የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን የከተማዋን የመጠጥ ውኃ ችግር ለመፍታት 2.2 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል አለ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3h ago
4:17
5