Search
ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው አመለካከት ምን መሳይ ነው? by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው አመለካከት ምን መሳይ ነው?
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው አመለካከት ምን መሳይ ነው?
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ጥቅምት 21 2018
ከ3 ዓመታት ወዲህ የሚታየው የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ላይ ያሳደረው የስነ ልቦና ጫና ተስፋ እስከመቁረጥ የደረሰባቸው መሆኑን ተማሪዎች ይናገራሉ፡፡
በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተማሪው፣ በትምህርት ባለሞያው እንዲሁም በተማሪ ቤተሰቦች ቅሬታ እያስነሳ ነው፡፡
ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው አመለካከት ምን መሳይ ነው? ስንል በጠየቅንበት ወቅት ቤተሰብ ልጆቻቸው እንዲማሩላቸው ስለሚፈልጉ አልያም አልተማሩም ላለመባል ብቻ ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ተናግረዋል፡፡
ይህንን ሀሳብ የሰማነው ከዘንድሮ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ነው፡፡
ተማሪዎቹ አሁን ላይ ለትምህርት ስላላቸው ፍላጎት እና እያስተናገዱት ስላለው ስሜት ምን ይጠቁመናል? ስንል ባለሞያ አነጋግረናል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እቅድ እና ስራ አመራር ትምህርት ክፍል ባልደረባ ዶክተር ደሞዜ ደገፋ አሁን እየታየ ያለው የ12ተኛ ክፍል ውጤት መውረድ በትምህርት ላይ ያሉትን ተማሪዎች የመማር ፍላጎታቸው እንዲቀንስ እና ተስፋ እንዲቆርጡ ያደርጋቸዋል ይላሉ።
የፈተና ውጤቱ ችግር መኖሩን አሳይቷል የሚሉት ደሞዜ(ዶ/ር) ተማሪው ይኮርጅ ነበር የሚለው ላይ ብቻ ከማተኮር በአግባቡ የሚማሩበት ሁኔታ አለ ወይ? ብቁ መምህራን አሉ ወይ? የሚለው መፈተሽ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1h ago
4:38
0
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
5h ago
3:13
6
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
5h ago
2:33
1
በትምህርት ሥርዓቱ አይነ ስውራን ከማይማሯቸው የት/ት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀት የሚያገኝበት አይሲቲ አንዱ ነው፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
6h ago
5:07
3
ከዚህ ቀደም በገላን ሁለገብ ደረቅ ወደብ የደረሱ እቃዎችን እዛው የጉምሩክ ሥርዓት ማስፈፀም ሲገባ ለጉምሩክ ሥርዓት ሲባል ብቻ ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ እቃዎች በከባ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
6h ago
4:57
26