Search
ኢትዮጵያ መድሀኒት የምትቆጣጠርበት ስርዓቷ በአለም ጤና ድርጅት ተመዝኖ አንድ ደረጃ ማሻሻሏ ተነገረ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
ኢትዮጵያ መድሀኒት የምትቆጣጠርበት ስርዓቷ በአለም ጤና ድርጅት ተመዝኖ አንድ ደረጃ ማሻሻሏ ተነገረ
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ኢትዮጵያ መድሀኒት የምትቆጣጠርበት ስርዓቷ በአለም ጤና ድርጅት ተመዝኖ አንድ ደረጃ ማሻሻሏ ተነገረ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
መስከረም 23 2018
ኢትዮጵያ መድሀኒት የምትቆጣጠርበት ስርዓቷ በአለም ጤና ድርጅት ተመዝኖ አንድ ደረጃ ማሻሻሏ ተነገረ፡፡
ኢትዮጵያ በአለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገራት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካላት ምደባ(Classification) ማቹሪቲ ሌቭል ስሪ (ደረጃ 3) ላይ መድረሷ ተነግሯል፡፡
ይህ እውቅና የበዙ ጠቀሜታዎች ያሉት እንደሆነ፤ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን እና ጤና ሚኒስቴር በሰጡት የጋራ መግለጫ ላይ አስረድተዋል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት ኦዲተሮች በስምንት ተግባራት ላይ የሰነድ ግምገማ ተደረጎ ጥሩ የሚባል አፈፃጸም በማግኘታቸው ነው ይህ እውቅና የተገኘው ሲሉ የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ(ዶ/ር) በመድረኩ ተናግረዋል፡፡
ይህ ውጤትም ተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት፤ ለሕብረተሰቡ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ውጤታማ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የህክምና ምርቶችን ለማቅረብ የሚረዳው እና የሚያበረታው እንደሆነም የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ መድሀኒት የምትቆጣጠርበት ስርዓቷ በህዝብ አመኔታ እንዲኖረው ይህ እውቅና እንደሚረዳም በመድረኩ ተነስቷል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:00
8
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:30
4
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
4:38
4
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
3:13
7
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
2:33
2