Search
ኢትዮጵያ እስካሁን የተመዘገቡት አጠቃላይ የፈጠራ ውጤቶችና የንግድ ምልክቶች ከ51,500 ያልበለጡ ናቸው ተብሏል by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
ኢትዮጵያ እስካሁን የተመዘገቡት አጠቃላይ የፈጠራ ውጤቶችና የንግድ ምልክቶች ከ51,500 ያልበለጡ ናቸው ተብሏል
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ኢትዮጵያ እስካሁን የተመዘገቡት አጠቃላይ የፈጠራ ውጤቶችና የንግድ ምልክቶች ከ51,500 ያልበለጡ ናቸው ተብሏል
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
መጋቢት 12 2017
በኢትዮጵያ ያሉ አብዛኞቹ የፈጠራ ባለቤቶች ስራቸውን ለማስመዝገብ ዳተኛ በመሆናቸው ለንጥቂያ እየተጋለጡ መሆኑን የኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ተናገረ፡፡
የአዕምሮ ውጤት የሆኑ የፈጠራ ስራዎችንና የንግድ ምልክቶችን የሚመዘግበው ባለስልጣኑ መመዝገብ ካለበት አንፃር እንዲመዘገብ የሚቀርብልኝ ጥቂቱ ነው ብሎናል፡፡
ኢትዮጵያ ባለብዙ የፈጠራ ባለቤቶች ሃገር ብትሆንም እንካሁን የተመዘገቡት አጠቃላይ የፈጠራ ውጤቶችና የንግድ ምልክቶች በደምረው ከ51 ሺህ 500 ያልበለጡ ናቸው ብሏል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ የንግድ ምልክቶች 34ሺህ ናቸው ማለትም 18ሺህ ያህሉ የሃገር ውስጥ ንግድ ምልክቶች 16ሺህ ደግሞ በኢትዮጵያ የሚሰሩ የውጭ ሃገራት የንግድ ድርጅቶች ናቸው፡፡
ኮፒራይት (ቅጂና ተዛማች መብቶች) በሚለው ዘርፍ የተመዘገቡት የኪነጥበብ ስራዎች 9ሺህ፤ ፓተንት በሚለው ስር የተመዘገቡት አዲስና የተሻሻሉ ፈጠራ ስራዎች ደግሞ 8ሺህ 500 ናቸው ያሉን በኢትዮጵያ የአእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ኤሊያስ መሃመድ ናቸው፡፡
የፈጠራ ስራዎች ባለመመዝገባቸው ስራዎቹ ተሰረቁብን፣ የምርት ምልክታችን ተመሳስሎ ተሰራ የሚሉ ቅሬታዎች ይመጣሉ የሚሉት አቶ ኤሊያስ ጉዳያቸውን ወደ ፍርድቤት ወስደው መብታቸውን እንዲያስከብሩ እንደግፋቸዋለንም ይላሉ፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4