Search
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በቱሪዝም ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት አድርጎ በምክር ቤቱ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ ፈቃድ ሰጥቷል by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በቱሪዝም ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት አድርጎ በምክር ቤቱ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ ፈቃድ ሰጥቷል
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በቱሪዝም ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት አድርጎ በምክር ቤቱ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ ፈቃድ ሰጥቷል
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
የሚኒስትሮች ምክር ቤት 53ተኛ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት በቱሪዝም ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት አድርጎ በምክር ቤቱ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡
ኢትዮጵያ የቱሪዝም ፖሊሲዋን ለመጨረሻ ጊዜ ያሻሻለችው በ2001 ዓ.ም ነበር፡፡
ታዲያ አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ በውስጡ ምን ይዟል? ስንል በፖሊሲ ማርቀቁ ላይ የተሳተፉትን አቶ ኤንዲ አሰፋን ጠይቀናቸዋል፡፡
የቱሪዝም ባለሙያው አቶ ኤንዲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ወደ ስራ እንዲገባ የተፈቀደው አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ በዘርፉ ከዚህ ቀደም ይነሱ ለነበሩ ችግሮች ምላሽ ይዞ መጥቷል ይላሉ፡፡
ከዚህ ቀደም ቱሪዝም መሰረተ ልማትን በተመለከተ በፖሊሲ ደረጃ የተቀመጠ ነገር አልነበረም አዲሱ ፖሊሲ በዚህ ዙሪያ ምላሽ አለው በዘርፉ የተማሩ ባለሙያዎችም እንዴት መሰማራት እንዳለባቸውም መንገድ አስቀምጧል ብለዋል፡፡
ይህም አሁን የተጀመሩ የቱሪዝም መሰረተ ልማቶች ልማትን የበለጠ እንዲጠነክር እገዛ ያደርጋል ይላሉ፡፡
የቱሪዝም ኢንቨስትመንት እንዴት መጠንከር እንዳለበት ፖሊሲው ምላሽ መያዙን የነገሩን አቶ ኤንዲ አሰፋ ከዚህ ቀደም ለውጪ ሀገር ቱሪስቶች የአደጋ ጊዜ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስጫ አሰራር አልነበረም አሁን ይህ አሰራር እንዲተገበር መንገድ ይከፍታል ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
የወጣው አዲስ ፖሊሲ በትክክል ከተተገበረ ጥሩ ለውጥ በዘርፉ ያመጣል የሚል እምነት አለኝ የሚሉት ባለሙያው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰላም ሁኔታ ቢመለስና ሀገራት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ዜጎቻቸው እንዳይንቀሳቀሱ የጣሉት የጉዞ ክልከላ ቢያነሱ ከፍተኛ የጎብኚ ቁጥር ኢትዮጵያ የማግኘት እድል አላት ብለዋል፡፡
በረከት አካሉ
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ኢትዮጵያ በመጪው አመት ከምታዘጋጀው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በተጓዳኝ ለሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውንና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ የሚያተኩር ዓለም አቀፍ አውደ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2h ago
4:42
4
በሀብት ሽሚያ ምክንያት በተለይ ጋምቤላ አካባቢ በነዋሪው እና በአካባቢው በተጠለሉ ስደተኞች መካከል ግጭት የተፈጠረባቸው ተደጋጋሚ ክስተቶች መታየታቸው ይነገራል
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3h ago
3:38
1
የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው እና ቀዳሚው ነፃ የንግድ ቀጠና ሆኖ ስራ ከጀመረ ከአራት አመት በላይ ሆኖታል።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
4h ago
5:37
4
ለትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘርነት ወንድ እና ሴት ተወዳዳሪዎች እኩል ውጤት ካመጡ ለሴት ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ እንድታልፍ የሚያደርግ መ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
5h ago
3:45
3
የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን የከተማዋን የመጠጥ ውኃ ችግር ለመፍታት 2.2 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል አለ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
5h ago
4:17
8