Search
በኢትዮጵያ ከሚከሰተው ዓይነ ስውርነት በግላኮማ የሚመጣው ቀዳሚው መሆኑ ተነገረ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
በኢትዮጵያ ከሚከሰተው ዓይነ ስውርነት በግላኮማ የሚመጣው ቀዳሚው መሆኑ ተነገረ
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ ከሚከሰተው ዓይነ ስውርነት በግላኮማ የሚመጣው ቀዳሚው መሆኑ ተነገረ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
መጋቢት 4 2017
በኢትዮጵያ ከሚከሰተው ዓይነ ስውርነት በግላኮማ የሚመጣው ቀዳሚው መሆኑ ተነገረ፡፡
ግላኮማ ሲከሰት ለረጅም ጊዜ ምልክት ለማሳየቱ ብዙዎችን ላይነ ስውርነት እየዳረገ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ዓለም አቀፍ የግላኮማ ሳምንት በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየታሰበ ነው፡፡
በግላኮማ ምክንያት የሚደርሰውን የዓይን ብርሃን ማጣት ለመከላከልም የዓይን ግፊትን በየጊዜው መከታተል እና ምርመራ ማድረግ ይገባል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ በቅርብ የተሰራ ጥናት ባይኖርም ከ 19 ዓመት በፊት በነበረው መረጃ በሌሎችም ምክንያቶች የሚፈጠር ዓይነት ስውርነት ውስጥ በግላኮማ የሚከሰተው ቀዳሚ መሆኑን የነገሩን የዓይን ሀኪም እና የግላኮማ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ናሆም አያሌው ናቸው፡፡
አሁን ባለው መረጃ በአለም ደረጃ 80 ሚሊዮን የሚያክል ህዝብ ወይም ሰው በግላኮማ ተጠቂ እንደሆነ ያሳያል፤ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገራት ላይ ግላኮማ በስፋት እንደሚታይ የሚናገሩት ዶክተር ናሆም ከአንድ ሚሊዮን ዜጎች ውስጥ 10 ሺህ ያህሉ በግላኮማ እንደሚያዙ ጥናት ያሳያል ይላሉ፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4