Search
ኢትዮጵያ 34ኛውን የአረጋዊያን ቀን ያከበረች ቢሆንም እስካሁን የአረጋዊያንን ማህበራዊ ዋስትና የተመለከተ አዋጅ ሆነ ፖሊሲ የላትም by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
ኢትዮጵያ 34ኛውን የአረጋዊያን ቀን ያከበረች ቢሆንም እስካሁን የአረጋዊያንን ማህበራዊ ዋስትና የተመለከተ አዋጅ ሆነ ፖሊሲ የላትም
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ኢትዮጵያ 34ኛውን የአረጋዊያን ቀን ያከበረች ቢሆንም እስካሁን የአረጋዊያንን ማህበራዊ ዋስትና የተመለከተ አዋጅ ሆነ ፖሊሲ የላትም
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
መስከረም 30 2018
በኢትዮጵያ 6.8 ሚሊየን አረጋዊያን ቢኖሩም የጡረታ አበል የሚከፈላቸው ግን 700,000 እንደሆኑ ተነግሯል።
በዚህም ምክንያት የኑሮ ውድነቱ ተጨምሮበት አብዛኞቹ አረጋዊያን የማምሻ ዕድሜአቸውን በችግር እየገፉ ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ክፍሉ ኬንያን ጨምሮ ሌሎች ሃገራት ዕድሜአቸው ከ60 በላይ ለሆኑ ሁሉም አረጋዊያን የጡረታ መብት ይከበርላቸዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ግን በተለይ ዕድሜውን ሙሉ በጉልበት ሥራ የሚገፋው ሁሉም ገበሬ ማለት በሚቻል ደረጃ የእርጅና ዘመኑ ከማህበራዊ ዋስትና ጥበቃና የጡረታ መብት ውጪ እንደሆነ ነግረውናል።
ይህ እንዲስተካከል ማህበራቸው ለዓመታት መንግስትን ቢጠይቅም የመንግስት ምላሽ ግን አረጋዊያኑ በወጣትነት ዕድሜአቸው የጡረታ መዋጮ ስላላዋጡ ነው የሚል እንደሆነ ኃላፊው ነግረውናል።
አረጋዊያን በወጣትነታቸው የጡረታ መዋጮ አዋጡትም አላዋጡም እንደ ሌሎች ሃገራት የጡረታ መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል የሚሉት ኃላፊው ይህም ከሃገሪቷ ኢኮኖሚ አቅም በላይ አይደለም ብለዋል።
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአረጋዊያንና ቤተሰብ ጉዳይ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሮበሌ በበኩላቸው መንግስት አቅም በሚፈቅደው ሁሉ የአረጋዊያን ማህበራትን ያግዛል፣ ወደፊትም ይህንን የተመለከተ አዋጅ ለማውጣት እየሰራን ነው ብለዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘንድሮ ለ35ኛ ጊዜ በሚከበረው የአረጋዊያን ቀን ኢትዮጵያ አንድ ዓመት ብቻ ዘግይታ 34ኛውን የአረጋዊያን ቀን ያከበረች ቢሆንም እስካሁን የአረጋዊያንን ማህበራዊ ዋስትና የተመለከተ አዋጅ፣ ስምምነትም(convention) ሆነ ፖሊሲ የላትም።
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3h ago
4:38
0
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
6h ago
3:13
6
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
6h ago
2:33
1
በትምህርት ሥርዓቱ አይነ ስውራን ከማይማሯቸው የት/ት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀት የሚያገኝበት አይሲቲ አንዱ ነው፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
7h ago
5:07
3
ከዚህ ቀደም በገላን ሁለገብ ደረቅ ወደብ የደረሱ እቃዎችን እዛው የጉምሩክ ሥርዓት ማስፈፀም ሲገባ ለጉምሩክ ሥርዓት ሲባል ብቻ ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ እቃዎች በከባ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
7h ago
4:57
27