Search
ኢንቨስትመንት ውስጥ መሰማራቱን ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ተናገረ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
ኢንቨስትመንት ውስጥ መሰማራቱን ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ተናገረ
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
ኢንቨስትመንት ውስጥ መሰማራቱን ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ተናገረ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
መጋቢት 22 2017
የራሱን የኢኮኖሚ አቅም የሚያዳብር ለሌሎችም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሊሰራ የሚችል ኢንቨስትመንት ውስጥ መሰማራቱን ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ተናገረ፡፡
ግብረ ሰናይ ድርጅት የሆነው ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ከለጋሾች ጥገኝነት ለመላቀቅ ያግዙኛል ባላቸውንና ወጪያቸውን በራሳቸው በሚሸፍኑ ሁለት የእናቶችና ህፃናት የህክምና ማዕከላት በወር ከ9ሺ በላይ ደምበኞችን እያስተናገደ መሆኑን ነግሮናል፡፡
በኢንቨስትመንት ውስጥ ልንሰማራ የቻልነው ባለፉት 6ዓመታት ስንሰራ በቆየንበት የሶሻል ቢዝነስ ሞዴል ነው የሚለው ድርጅቱ በግብረሰናይ ድርጅቶች ዘንድ ባልተለመደ አኳኋን የራሳቸውን ገቢ በሚያመነጩ በተለይም ፒያሳ አካባቢ ባለው አራዳ ቅርጫፍና 22 ቅርጫፍ የጤና ማዕከሉ ድርጅቶቹ የሚሰጠውን አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እዩልኝ ብሏል፡፡
የስነ ተዋልዶ ጤና፣የቅድመ እና ድህረ ወሊድ አገልግሎትና የህፃናት ህክምና የሚሰጥባቸው ማዕከላቱ አሁን ያለውን የህክምና ዋጋ ውድነት ታሳቢ በማድረግ በመንግስት የጤና ተቋማት ከሚከፈለው ከፍ ባለ፤ በግል የጤና ተቋማት ከሚጠየቀው በቀነሰ ተመጣጣኝ በሚለው ዋጋ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ኤም ኤስ አይ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር አበበ ሽብሩ ጠቅሰዋል፡፡
ይህ የቢዝነስ ሞዴል ከትርፍ ይልቅ ማህበራዊ ሃላፊነትን በመወጣት የራስን ገቢ ማመንጨት ላይ ያተኩራል የሚሉት ሃላፊው ከእነዚህም በተጨማሪ በመላው ሃገሪቱ ባሉት 21 መሰል ማዕከላት በሚሰጠው አገልግሎት ከሚያገኘው ገቢ ባለፉት ዓመታት 82 ሚሊዮን ብር መለንግስት ታክስ መክፈሉንም አንስተዋል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4