Search
የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ብሄራዊ የሚዲያ ሽልማት ለመስጠት የሚያስችለውን ጥናት ይፋ አድርጎ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ብሄራዊ የሚዲያ ሽልማት ለመስጠት የሚያስችለውን ጥናት ይፋ አድርጎ
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ብሄራዊ የሚዲያ ሽልማት ለመስጠት የሚያስችለውን ጥናት ይፋ አድርጎ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
መጋቢት 10 2017
ለመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች የሞያ ብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት እየተዘጋጀ መሆኑን የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ተናገረ።
ሚዲያው ላይ ያሉ ባለሞያዎችን መዝግቦ የሞያ ብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት የሚያስችለውን ጥናት ማድረጉን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ተናግሯል።
102 የሚደርሱ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትን በአባልነት እንደያዘ የሚናገረው ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ምን ያህል ጋዜጠኞች እንዳሉ ለማወቅ ከመመዝገብ ጀምሮ የሞያ ብቃት ማረጋገጫ መታወቂያ መስጠት ያስፈልጋል ብሏል።
የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤቱ ይህንን ስራ ለመስራት እንዲያግዘው ያደረገውን ጥናት ይፋ ያደረገበትና ከባለሙያዎች ምክረ ሃሳቦችን የሰበሰበበት ውይይት አድርጓል።
በዚህም ወቅት የምክር ቤቱ ስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ታምራት ሃይሉ፤ ለባለሙያው የብቃት ማረጋገጫ መታወቂያ መስጠት ያስፈለገው የጋዜጠኛውን ደህንነት ለመጠበቅ፣ ከጥቃት ለመከላከል እንዲሁም ከጫና ውጪ ሆኖ እንዲሰራ ለማስቻል እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በጥናቱ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል የሆኑት አየለ አዲስ(ዶ/ር) የብቃት ማረጋገጫውን ለመስጠት የተቀመጡ መስፈርቶችን ሲያብራሩ አመልካቹ በጋዜጠኝነት የትምህርት መስክ ከዲፕሎማ ጀምሮ ያለ የት/ት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
የስራ ልምድ፣ ለህዝብ የቀረበ ስራ ማቅረብ እንዲሁም የጋዜጠኝነት የስነምግባር ደንቦችንና የሃገሪቱን ህጎች ማክበር እንዳለበትም ጠቁመዋል።
የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የምክር ቤቱ አባል ለሆኑ ጋዜጠኞች እሰጠዋለሁ ያለው የሞያ ማረጋገጫ መታወቂያ፤ አባል ያልሆኑትን ስለ ማያጠቃልል ይህንን የማድረግ መብት የለውም የሚል ቅሬታ ከተሳታፊዎች ቀርቦበታል።
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:00
9
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
3d ago
2:33
4