Search
''በአቅሜ ልክ ግን እየሰራሁ አይደልም'' አምስተል ኢንቨስትመንት by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
''በአቅሜ ልክ ግን እየሰራሁ አይደልም'' አምስተል ኢንቨስትመንት
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
''በአቅሜ ልክ ግን እየሰራሁ አይደልም'' አምስተል ኢንቨስትመንት
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ነሀሴ 6 2017
አትክትልት እና ድራፍሬ ምርቶች ለረጅም ጊዜ ሳይበላሹ እንዲቆዩ በማድረግ ለገበያ እያቀረብኩ ቢሆንም በአቅሜ ልክ ግን እየሰራሁ አይደልም ሲል በዙርፉ የተሰማራው አምስተል ኢንቨስትመንት ተናገረ፡፡
ይህንን ስራ ለዓመታት እየሰራሁ ቢሆንም ዛሬም ድረስ በህብረተሰቡ ዘንድ እውቅና የለውም ብሏል፡፡
እንደ ካሮት፣ ድንች፣ ፎሶሊያ እና ሌሎች ፍራፍሬ እና አትክልቶች ተፀድተው እና ተከታትፈው በራሳቸው የሙቀት መጠን ፍሪጅ ውስጥ በማስቀመጥ ለምግብነት እንዲውሉ ማድረግ ላይ እንደሚሰራ ተናግሯል፡፡
እነዚህ ያለቀላቸው አትክልቶች የአመት እድሜ እንዲኖራቸው ተደርገው የተሰናዱ ናቸው ያሉት አምስተል ኢንቨስትመንት ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ እመቤት ታደሰ ምርቶቻችንን ለሆቴሎች እያቀረብን ነው ብለዋል፡፡
ፍራፍሬ እና አትክልቶች በዚህ ዓይነት መንገድ ተቀነባብረው ለአመት ሲቆዩ ተጠቃሚው ላይ ሊፈጥር የሚችለው የጤና ጉዳት ይኖር ይሆን? ስንል የጠየቅናቸው በአለም አቀፉ የምግብ ምርምር ፖሊሲ ኢንስቲቱት ተመራማሪ ሳይንቲስት የሆኑትን ዶክተር ታደሰ ዘርፉ እነዚህ ምርቶች ታሽገው ሲቀመጡ የራሳቸው በጎ ጎንም ቢኖራቸው ቢቻል ከቀናት ባዘል ካልሆነ ደግሞ ለተወሰኑ ከሳምንታት ብቻ ቢቀመጡ ጥሩ እንደሚሆን ምክረ ሀሳባቸውን ሰጥተውናል፡፡
ነገር ግን አትክልት እና ፍራፍሬዎቹ በእንዲህ ዓይነት መልኩ ታሽገው በቆዩ ጊዜ ተፈጥሮአዊ ይዘታቸውን እንዲቀይሩ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:00
8
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
2:33
3