Search
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የዳግም ምዝገባ እያደረገ ነው፡፡ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የዳግም ምዝገባ እያደረገ ነው፡፡
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የዳግም ምዝገባ እያደረገ ነው፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ሰኔ 17 2017
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የዳግም ምዝገባ እያደረገ ነው፡፡
እስካሁን እየተደረገ ባለው የዳግም ምዝገባ ሂደት፤ 85 የሚሆኑት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለዳግም ምዝገባው ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ጥሪ ቢደረግላቸውም አለመመዘናቸውና በዚህም ምክንያት ከዘርፉ መውጣታቸው ሰምተናል፡፡
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከዘርፉ የወጡበት ምክንያት ምን ይሆን? ሲል ሸገር ራዲዮ የግል ከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሞያ ተቋማት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁን ጠይቋል፡፡
ባለስልጣኑ እንደረገ ያለው የዳግም ምዝገባው የማይቃወሙት ሀላፊው፤ ነገር ግን የተቀመጡ መስፈርቶች አሳሪ እንደሆኑ ያብራራሉ፡፡
ከዘርፉ ከወጡ 85 ተቋማት ውስጥ 25ቱን ለማነጋገር ሞክረን ነበር ያሉን ሲሆን፤ አዲስ የወጣው የዳግም ምዘና መስፈርት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የሚከብዳቸው እንደሆም ያስረዳሉ፡፡
የግሉ ዘርፍ ከመንግስት የሚሰጠው ማበረታቻ የለም አሁን የወጣው አሠራር ደግሞ በአግባቡ ስራቸውን እንዳይሰሩ የሚያደርግ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ምከትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቢንያም ኤሮ በበኩላቸው፤ ከዘርፉ እየወጡ ያሉ ተቋማት ቢያንስ አነስተኛ የተባለውን መስፈርት እንዲያሟሉ ለማድረግ ድጋፍ ስናደርግ ነበር ብለዋል፡፡
የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ ሂደታችን ላይ ችግር ነበረብን ዳግም ምዝገባ ለማድረግ የተገደድነውም ይህንን ስህተት ለማረምና ብቁ ተቋም ለመፍጠር ነው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ስንል ነው እርምጃውን እየወሰድን ያለነው ሲሉም ነግረውናል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:00
8
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
2:33
3