Search
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ የትኛውም መስሪያ ቤት ለስልጠና የሆቴል ግዢ እንዳይፈጽም የሚከለክል ትዕዛዝ የፋይናንስ ቢሮ አሳልፏል by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixes.VuiZ.Net
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ የትኛውም መስሪያ ቤት ለስልጠና የሆቴል ግዢ እንዳይፈጽም የሚከለክል ትዕዛዝ የፋይናንስ ቢሮ አሳልፏል
By
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ የትኛውም መስሪያ ቤት ለስልጠና የሆቴል ግዢ እንዳይፈጽም የሚከለክል ትዕዛዝ የፋይናንስ ቢሮ አሳልፏል
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
0:00
0:00
Description
ነሀሴ 12 2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ የትኛውም መስሪያ ቤት ለስብሰባ፣ ለግምገማ እና ለስልጠና የሆቴል ግዢ እንዳይፈጽም የሚከለክል ትዕዛዝ የፋይናንስ ቢሮ አሳልፏል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ሁሉም የከተማ አስተዳደር ቢሮዎች እና ከፍለ ከተሞች ለሆቴል ኪራይ መክፈል አይችሉም ሲሉ ነግረውናል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ቢሮ ተፈርሞ ከወጣ ደብዳቤ ላይ እንደተመለከትነው በ2018 በጀት ዓመት ሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራቸውን ለመገምገምም ሆነ ለስልጣና ከበጀታው ላይ ለሆቴሎች እንዳይከፍሉ የሚከላክል ነው፡፡
መስሪያ ቤቶቹ ልዩ ልዩ ስብሰባዎችን፣ ስልጠና እና ግምገማዎችን ለማድረግ የመንግስት በየክፍለ ከተሞቻቸው የሚገኙ የመንግስት የመሰብሰቢያ አዳራሾችን እና ከፍቴሪያዎችን እንዲገለገሉ ያዛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት እቅድ መከወኛ 350.1 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን ያስታወሰው ቢሮው 70 በመቶ የሚሆነው ለካፒታል በጀት የተደለደለ መሆኑን አስታውሷል፡፡
ቀሪው ለመደበኛ ስራዎች መከወኛ መመደቡን ተናግው ይህን በጀት በእቅዱ መሰረት ስራ ላይ ለማዋል አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡
መስሪያ ቤቶቹም ይህን የተመደበላቸውን በጀት በቁጠባ እንዲጠቀሙም አሳስቧል፡፡
Direct Download
More from
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:00
8
የአፍሪካ የንግድ ስራዎች ትስስር ጉባኤን (ACCS) በአዲስ አበባ ለማካሄድ ሶስት የሙያ ማህበራት ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተ
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
1d ago
5:30
5
ብዙ ችግሮች አሉበት የሚባለውን የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ለማስተካከል ከተከወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር አንዱ ተግባር ቢሆንም እስካሁን
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
4:38
5
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሴት አመልካቾች ብቻ እንዲመለመሉ የሚያደርግ መመሪያ ወደ ስራ ገባ፡፡
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
3:13
8
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶች በአመት የሚገኘው ገቢ ወደ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር መቀነሱ ተነገረ።
ሸገር 102.1FM(ShegerFM)
2d ago
2:33
2